Ethiopia declares three days of national mourning on the Irrecha incident

Addis Ababa: (October 2, 2016): በተሻሻለው የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 863/2006 አንቀጽ 22 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት በሀገሪቱ ውስጥ አደጋዎች ሲፈጠሩም ሆነ አሳዛኝ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሀዘን መግለጫ ይደነግጋል ፡፡ ምክር ቤቱ በስራ ላይ ባልሆነበት ጊዜ የምክር ቤቱ አፈጉባዬ በምክር ቤቱ ስም የሀዘን ቀን እንደሚወስን አዋጁ ይደነግጋል፡፡

በዚሁም መሰረት የኦሮሞ ህዝብ የሰላም፤ የፍቅርና የምስጋና ቀን የሆነውን የኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ ፀረ-ሰላም ሀይሎች በፈጠሩት ሁከት ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ንጹሀን ዜጎች ለማሰብ ከነገ ጠዋት 12 ሰዓት ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ የ3 ቀናት ሀዘን ታውጇል፡፡

በዚሁም መሰረት ሁሉም የመንግስት ተቋማት ፤ በኢትዮጵያ ኤንባሲዎችና ቆንስላዎች፤ ትምህርት ቤቶች እና በኢትዮጵያ በተመዘገቡ መርከቦች የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ የሚውለበለብ ይሆናል፡፡

Source: Office of Federal Government Communication

Leave a Reply