ያለፈው ሳምንት ትኩሳትና ዳግም በርካታ ተመልካች ያገኙ የቪድዮ ምስሎች

በላይ አለምሰገድ – የመርካተው

የዚህ ፅሁፍ ርእስ ላይ ለመግለፅ እንደመኮርኩት ያለፈው ሳምንት ትኩሳት አፈራረጅ በተለያዩ ሃይሎች የተለያዩ ትርጉሞች ተሰጥተውት ሲፃፍበት ሰከን ብሎ ነገሮችን በማየት ላይ ያለው ህዝብ ምን ይል ይሆን ብየ ከጎንደር ከተማ ሰልፍ ብሃላ በአዳማና ባህርዳር ከተሞች በአውደ ጥናት ምክንያት በተገኘሁበት ወቅት የህዝብ ሁኔታ ለማስተዋል መክርያሎህ፡፡ በውሱን ከተሞች ወደ ብጥብጥና ሁከት ያመራው እንቅስቃሴ ባለቤት ይንሮውም አይኑሮም የአገር ጉዳይ ስለሆነ የተሳተፍኩባቸው አውደ ጥናቶች እያቋረጥክ ወጣ በማለት ወጣቶች በርከት ብለው በሚሰባሰቡበት አከባቢ ተገኝቼ በራሴ መንገድ ሁኔታውን ለመገንዘብ ሞክርያሎህ፡፡ በሚያስገርም መልኩ ተገቢ መረጃ ያለውና የሌለው የህብረተሰብ ክፍል የሚኖረው የሚዛናዊነት ልዩነት ቁልጭ አድርገው ያሳዩኝን ሁለት አጋጣሚዎች በቅድምያ ማውሳት እፈልጋሎህ፡፡ እንዲሁም ከዚህ ጋር በተያያዘ ህዝቡ ትክክለኛ መረጃ ፍለጋ እንዴት እንደሚባዝን የሚያመላክቱ ዳግም በርካታ ተመልካች ያገኙ ቪድዮዎችና የዚህ ውጤት ምክንያት ይሆናል ያልኩት ለመዳሰስ እሞክራሎህ፡፡

በአንድ ወገን እጅግ በእርጋታ የሚወያዩ ወጣቶች በብዛት በስራና በማህበራዊ ጉዳዮቻቸው በካፌዎች፣ የፑል መጫዎቻዎች የውጭ ስፖርት መከታተያ አዳራሾች በተገኸሁባቸው ስፍራዎች ካስተዋልኳቸው ጥቂት ስፍራዎች ናቸው፡፡ከዚህ በተለየ መልኩ አላስፈላጊ መልእክት እንዳያስተላልፍ በጥንቃቄ ስማቸው በማልጠቅሳቸው አዝማሪ ቤቶች ደግሞ በዚያ ሳምንት የነበረው ሁኔታ የተለየ ነበር፡፡ በነዚህ የአዝማሪ ቤቶች የተገኘ ሰው በማግስቱ ይሀ አገር ይቀጥል ይሆን ብሎ እስኪጠራጠር ድረስ ተደናቁሮ እንዲወጣ የሚያደርጉ ግጥሞች ከሁሉም ጫፎች ይዘንባሉ፡፡ እንዲሁ የባህል ጨዋታ አምሮት የገባ ሰው ሁሉ ሳያይፈልገው ያጨበጭባል፡፡ ከፋዩ የማይታወቅ መጠጥ ይቀርባል፡፡ ወጣቶች እየተበራከቱ ይሄዳሉ፡፡ ይህ ሁኔታ አዳማም አዲስ አበባም የመጠንና የቅኝት ለውጥ ካልሆነ በቀር ተመሳሳይ የመረጃ ፍስት ያለ በሚመስል መልኩ በተገኘሁባቸው አብዛኛዎቹ አዝማሪ ቤቶች ግጥሞቹ ይፈሳሉ፡፡ህዝብ እንደ ህዝብ ይሰደባል፡፡ባለስልጣን ይብጠለጠላል፡፡ አንዳንዱም በቅኔ ይወደሳል፡፡ እንደዚህ አይነት አጀንዳ በሌላቸው አዝማሪ ቤቶች ዶላር አይመነዘርም፡፡ ሽልማት እምብዛም ነበር፡፡በጥቅሉ ሞቅ ያለ ገበያ አልነበራቸውም፡፡ አስቀድመው የተፈረጁም ይመስላሉ፡፡

ምሽት እነዚህ ቦታዎች ቆይቼ ሌሊቱን መተኛት አስቸጋሪ ቢሆንም በማግስቱ ቀደም ብየ በገለፅካቸው ፑል ሃውስ፣ ዲኤስ ቲቪ በሚያሳዩና በካፌዎች አከባቢ ስዘዋወር የማታው አደንቋሪ አጀንዳ ብዙም አልሰማሁም፡፡ መደበኛ የኢትዮጰያ ቴሌቪዥንና የየክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዜና ስአት ላይ የሁሉም ሰው ቀልብ ይሳባል፡፡በአንድ የዲኤስ ቲቪ ማሳያ ቦታ ግን ዝጋ…ዝጋ…ዝጋ… የሚል የሁለት ወጣቶች ድምፅ የሁሉም ተመልካች ድምፅ ውጦ ታየ፡፡ እናም የስፖርት ቻናሎችን እየቀያየረ የሚያሳየው ወጣት ለቆይታ ብሎ አጫጭር የስፖርት ውጤቶችን የሚያሳይ ቻናል ሲያቀርብ በሁለቱ ወጣቶች የውዳሴ ጭብጨባ ተጀምሮ እዛው የታደመ አብዛኛው ሰው አጀባቸው፡፡

በአጠቃላይ በነዚህ አከባቢዎች ያስተዋልኩት የጤና እንዳልሆነ እያሰብክ ወደ አዲስ አበባ እንደተመለስክ በጎንደር የተጀመረ ሰልፍ ባህርዳርንና ደብረታቦርን አዳርሶ ወደ ሰፈሬ ሳይደርስ በመንግስትና ህዝብ ትብብር መክሸፉን በህዝብ መገናኛ ብዙሃን መስማት ጀመርክ፡፡ በመገናኛ ብዙሃንና እዛው በሚቀርቡ ባለስልጣናት ከባህርዳር በስተቀር (ሰማያዊ ፓርቲ) በሌሎቹ ከተሞች የተካሄዱት ሰልፎች ባለቤት አልነበራቸውም የሚል ነው፡፡ ይህ እጅግ የሚገርም አቀራረብ እንደዚህ አይነት መሰሪ ስራ ለሚሰሩት የልብ ልብ የሚሰጥ እኔን ጨምሮ ዜጎችን ግራ የሙያጋባና በህዝብ ተሳትፎና ብርታት አውዳሚ የሆኑ እንቅስቃሴዎች እንዳይመክኑ የሚያደርግ ነበር፡፡ በተግባርም ከነዚህ ከተሞች በተጨማሪ በትናንሽ ከተሞች ሙሉ ለሙሉ የመንግስት ንብረት ወደ ማውደም የተሸጋገረውም ለዚሁ ይመስላል፡፡

ህዝቡ ያልተፈቱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንደሚኖሩት ጥርጥር የለኝም፡፡ ነገር ግን ይህን የህዝቡ ጥያቄ በመቀልበስ ለራሳቸው የፖለቲካ መሳርያነት የተጠቀሙበት ሃይሎች በድፍረት ያለመኮነን ችግር ምን አመጣው? እንቅስቃሴዎቹ በመሳርያ የተደገፉ ናቸው ካልን ኢትዮጰያ በአሸባሪነት የፈረጀቻቸው የግዛት አንድነት በትጥቅ ትግል አስመልሳሎህ የሚለው ግንቦት 7ና ኦሮምያን ገንጥየ የግል ንብረቴ አደርጋሎህ ብሎ ታጥቆ የሚንቀሳቀሰ ኦነግ በህዝቡ ጥያቄዎች ሰበብ ጀሌዎቻቸው አሰማርተውና በማህበራዊ ድረ ገፅና ቪኦኤ እየመሩት የተካሄደ መሆኑ ደፍሮ መናገር እንዴት ያቅታል? እንዴትስ ከዚህ ጀርባ ሻእብያ መኖሩን ማሳወቅና ማጋለጥ ሲገባ ዳር ዳሩን መዞር ለምን አስፈለገ ?

ተመሳሳይ ሁኔታ በማይታይባቸው አሸባሪዎችን አስቀድመው በቁጥጥር ስር ያዋሉና መሳርያ አንግተው የወጡ ወገኖቻቸውን መክረው የመለሱ የሶማሌና አፋር ክልሎች ያህል ድፍረት እንዴት ይታጣል? እነዚህ ክልሎች እንቅስቃሴው የኦብነግና የሻእብያ ነው ብለው መሪዎቻቸው በግልፅ ወጥተው ተናግረዋል፡፡ እንዲሁም ወደ አዲስ አበባ ይገባ የነበረን በጦር መሳርያ የተደገፈ ህገ ወጥ ቡድን የያዘው የአዲስ አበባ ዙርያ የኦሮምያ ነዋሪና የፌደራል መንግስቱ መግለጫዎች ግልፅና የማያሻማ ነበር፡፡ ኦነግ ያደራጃቸው ስብስቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ግልፅ መረጃ ለህዝቡ አቅርበዋል፡፡ በነገራችን ላይ ሰሞኑን በዓይጋ ፎረም ወጥቶ ያየሁት የዋሽንግተን ሰላማዊ ሰልፍ ፎቶግራፍ የሻእብያ ስብስብ ከነባንዲራቸውና ልሙጡ የግዛት አንድነት የኢትዮጰያ ባንዲራ የያዙ የግንቦት 7 ሌሎች የኢትዮጰያ ጠላቶች በተስፋ መቁረጥ ስሜት በግላጭ አደባባይ አንድ መሆናቸው ያስመሰከሩበት አጋጣሚ ነው፡፡

መሆን የነበረበት ተመሳሳይና የተናበበ ጠላቶችን የማጋለጥ ስራ ቢሆንም ይህ ሲደረግ አላስተዋልኩም፡፡ ወጣቱ በአንዳንድ ጉዳዮች ግልፅ እንዲሆኑለት ድረ ገፆችን በመበርበር ወደ ሀላ መለስ ብሎ መረጃዎች ለማግኘት መሞከሩም ለዚህ ነው፡፡ ከነዚህም መካከል ህዝብን ከህዝብ ጋር በማጋጨት የኢትዮጰያ ጠላቶች ይህችን አገር ለማፈራረስ ከተጠቀሙባቸው አጀንዳዎች ውስጥ እውነታውን በራሱ መንገድ ለማረጋገጥ ሞክሯል፡፡ዶላር እየተመነዘረ ሽልማት ይበተንባቸው በነበሩ አንዳንድ የአዝማሪ ቤቶች ግጥሞች ወስጥ በዋናነት ህዝብን በመሳደብ ይገለፁ የበሩትን ብልግናዎች ቃል በቃል መግለፁ ከተናጋሪው ደጋሚው ስለሚሆን ልተወው፡፡ ነገር ግን ለምን እንዲህ አይነት ጥላቻን ያዘለ አስተሳሰብ በነዚህ ሰልፎች ላይ ታየ በሚል ወጣቱ ጎርጉሮ ካወጣቸው ቪድዮዎች ውስጥ በኢትዮጰያ ብሮድካስት ኮርፖረሽን የተላለፈውና ከ2ሺ በላይ ተመልካች ያልነበረው አንድ የቪድዮ ዜና አርካይቭ በአንድ ግዜ 93ሺ መድረሱ ነው፡፡ ከዚህ ቪድዮ ጋር የሚቀራረቡ ሶስት ቪድዮዎች በተመሳሳይ በአስርሽዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተመልክተዋቸዋል፡፡ ቪድዮዎቹን ለማየት ለጓጓቹህ በቅድምያ ይህን ሊንክ ተጭናቹህ ማየት ትችላላቹህ የዚህ ሁኔታ ትርጉምና ሁኔታውን ለመገንዘብ ለሚጣጣረው ወጣት ደግሞ አስቀድሜ ላመስገንና ወደ ዝርዝር ሃሳቤ ልግባ፡፡

ኢትዮጰያውነት በፅኑ መሰረት ላይ የተገነባው ፌደራላዊ ስርአት ያላት በመሆኑ የሚያጋጥሙት ፈተናዎች የማለፍ ብቃትዋ ከነዚህ ሁኔታዎች በላይ ሌላ ማረጋገጫ የለም፡፡ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ለዘመናት ባደረጉት ተጋድሎ አምባገነንንና ሃላቀር አስተሳሰቦችን አሸንፈው በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተች የኢትዮጰያ ፌደራላዊት ዴሞክራሲያዊት ሪፓብልክን መመስረት ችለዋል፡፡ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች በከፈሉት መስዋእትነት የሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘብ አንድ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ማህበረሰብ መገንባትን ግባቸው አድርገው ያፀደቁት ህገ መንግስት ግንዛቤ እየተጠናከረ በመሄድ ላይ ነው፡፡

የኢትዮጰያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በህገ መንግስቱ የተቀመጡ ድንጋጌዎች በማክበርና በማስከበር ያደረጉት ሰፊ ጥረት ፌደራላዊ ስርአታችን በፅኑ መሰረት ላይ የተገነባ መሆኑ ለወዳጅም ለጠላትም የሚያስገነዝቡ በርካታ ፈተናዎች አልፏል፡፡ በተለይም ባለፉት አምባገነናዊ ስርአቶች ከፋፍሎ የመግዛት ኋላቀር መርህ ሊሳካ ያልቻለው በህዝባችን የቆየ ተቻችሎ የመኖርና የማስተዋል እሴት መሆኑ ሊማሩ ያልቻሉና የማይፈልጉ ፅንፈኛ ሃይሎች ከኋላ ቀር ስርአቶች መደምሰስ ብኋላም በሰበብ አስባቡ ህዝብን በመተንኮስ ሀገር ለማተራመስ ያደረጉት ሙከራ መምከኑ ይታወሳል፡፡

እንዲህ አይነት ሰው ሰራሽ ፈተናዎች ሳይቀር በማለፍ ሀገራችን በሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ ህዝባችን ያረኩና ሀገራችን በአለም አቀፍ ደረጃ ስምዋን የሚያስጠሩ ድሎች እያስመዘገበች ቀጥላለች፡፡ ፌደራላዊ ስርአታችን ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው እያስተዳደሩ ጠንካራና ዴሞክራሲያዊ ሀገር ለመገንባት የሚያደርጉት ጉዞም በአስተማማኝ ጎዳና ላይ ይገኛል፡፡ ለዚህ የጋራ መግባባት መሰረት የሆነው ህገ መንግስት ያስቀመጣቸው መርሆዎች በላቀ ደረጃ በመተግበር የኢትዮጰያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች እያከናወኑት ባለ መጠነ ሰፉ እንቅስቃሴ በርካታ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ድሎችም ተገኝተዋል፡፡እንዲሁም ከውስጥ ሰላምዋ ማስጠበቅ አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ የሰላም ማስከበር ግዳጅን በብቃት የምትወጣና እጅግ ፈጣን በሆነ የኢኮኖሚ እድገትዋ የምትታወቅ ሀገር ሆናለች፡፡

ይሁንና በህዝቦች ግጭት ወደ ስልጣን የመምጣት አባዜ የተጠናወታቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ከውጭ የኢትዮጰያ ጠላቶች ጋር በማበር በተደጋጋሚ ስርአቱን ለመፈታተን የሚያደርጉት ሙከራ አሁንም አላቋረጠም፡፡ እነዚህ ቡድኖች የሚያደርሱት ጉዳት እንዲቀንስ ለማድረግና በተስፋ መቁረጥ ስሜት እየተነዱ ሊፈጥሩት የሚያስቡት የህዝቦች መቃቃር ማስቀረት እየተቻለ ያለው በህዝቡ ውስጥ ለዘመናት የቆየው የብህዝሃነት በጎ እሴት ህገ መንግስታዊ መሰረት እንዲይዝ በማድረግ የዴሞክራሲያዊ አንድነት ጉዞ ተጠናክሮ በመቀጠሉ ነው፡፡ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የፀረ ድህነት ትግላችን መሰረት በማድረግ የተቀረፁ ሁሉን አቀፍ አጀንዳዎች ላይ የሚፈጠሩት ሀገራዊ የጋራ መግባባቶች ከግዜ ወደ ግዜ እየተጠናከረ መሄድ በእነዚህ ሃይሎች የሚደረጉ ማናቸውም እንቅስቃሴዎች ትርጉም አልባ እንዲሆን አስችሏል፡፡

መንግሰታችን ቀድሞም ቢሆን በአገር ውስጥና የውጭ አሸባሪ ሃይሎች ሊደርስ የሚችል አደጋ በላቀ የህዝባችን ተሳትፎ እንዲገታ ተገቢ የፀረ ሽብር ህግ በማውጣት ተግባራዊ በማድረጉ በአለም አቀፍ ደረጃ ተመሳሳይ የጥፋት ሃይሎች እያደረሱ ያሉት መጠነ ሰፊ ጉዳት በአገራችን እንዳይደርስ የሚያስችል ተቋማዊ ብቃት ገንብቷል፡፡

አሸባሪ የጥፋት ሃይሎች በሚያሳዩት ተቀያያሪ ባህሪ፣ በሚያፈሱት መዋእለ ንዋይ መጨመርና የሚጠቀሙባቸው የሽብር መረቦች መስፋፋት ምክንያት በሰው ሂወትና ንብረት ላይ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ በኤርትራና በአንዳንድ የውጭ አገራት የተጠለሉት አሸባሪዎችና ሁከት ፈጣሪዎች ወደ ስልጣን ይመጡ ዘንድ ህዝብ እንዲተላለቅ ለማድረግና ኢትዮጵያን ለማተራመስ ሳይተኛ የሚያድረው የኤርትራው ህግደፍ ችግሩ ከቁጥጥር ውጭ የወጣ ለማስመሰል በኢትዮጰያውያን ስም የሃሰት ታርጋ በለጠፉ የሻዕብያ አባላት በከፈትዋቸው ማህበራዊ ድረ ገፆችና ቅጥፈቶቻቸው በሚያራግቡ ፅንፈኛ ሚዲያዎች አማካኝነት የከፈቱት ዘመቻ ጫፍ ደርሷል፡፡
በዚህ መሰረት ለዘመናት አብሮ በኖረው፣ ምንጊዜም የማይፋቅ ወንድማማችነት ባለው ህዝብ መካከል ቁርሾና መቃቃር በመፍጠር ሁከቱ እንዲቀጥል ለማድረግ ለእንደዚ አይነት ቅጥፈት እንዲያመች አንዳች ምልክት እንኳን ሳይኖር በየድረ ገፁ የፈጠራ ድርሰቶችና የሌላን አገር የብጥብጥና ሁከት ጠባሳ የሆኑ ዘግናኝ ምስሎች እየለጠፉ ህዝብ ውስጥ መርዝ ሊዘሩ ሞክረዋል፡፡
ይህም ሆኖ የአጥፊ ሃይሎች ቅጥፈትና ጥፋት እንዲገታ በማድረግ ረገድ የፌደራል መንግስት፣ ብሄራዊ ክልሎች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ ህዝቡና ሙሁራን በጋራና በተናጠል እየወሰድዋቸው ያሉ አቋሞች በፅኑ መሰረት ላይ የተገነባው ፌደራላዊ ስርአታችን ሁሉንም ፈተናዎች የማለፍ ብቃቱ እያስመሰከረ መቀጠሉ የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡ የኢትዮጰያ ህዝቦች ህገ መንግስታዊ ስርአቱን የመጠበቅ ጥንካርያቸው በማደርጀት በዘረኝነት ያበዱ የሻእብያ መንግስትና ተላላኪዎቹ ትግል አጠናክረን በመቀጠል አቻ ያተገኘለትና የኢትዮጰያን የዘመናት ለቅሶ ያስቆመው ፌደራሊዝም እንደ አይናችን ብሌን ልንከባከበው ይገባል እላሎህ፡፡ ሰላም ለሁላችን፡፡

3

Leave a Reply