የህዝቦች ግጭት ምኞት እንጂ እርግጠኛ ሆኖ አያውቅም-አይሆንምም­

ያሬድ አለምሰገድ

ሰሞኑን በጎንደር ከተማና አከባቢው ባለ ግርግር ተጠቅመው ህዝብን በማጋጨት ምኞት  ፅንፈኛ ሃይሎችና በማወቅም ሆነ በማለማወቅ በነሱ ጥላ ስር የተጠለለ ጊዚያዊ ስብስብ ነዋሪዎችን በመተንኮስና በማህበራዊ ድረ ገፆችና እንደ ቪኦኤ የመሰሉ መዋግያ መሳርያዎች ቢጠቀሙም ጠብ የሚል ነገር አላገኙም፡፡ በህገ ወጥ ተግባር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋል ያለባቸው ግለሰቦችም በህግ ጥላ ስር እንዲውሉ ከማድረግ አላስጣልዋቸውም፡፡ እርግጥ ነው የፀጥታ ሃይሎችና ሰላማዊ ዜጎችም ላይ ጉዳት መድረሱ አልቀረም፡፡ ለህግ ልዓላዊነት መከፈል ያለበት የተከፈለ መስዋእትነት ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል፡፡

ከዚህ በላይ ያለው ድንቅ ነገር  ፅንፈኛ ሃይሎችና በማወቅም ሆነ በማለማወቅ በነሱ ጥላ ስር በጊዚያዊ ስሜት የተጠለለው ስብስብ ከጎንደርና አከባቢው ህዝብ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ ከነዚህ መካከል ጎልቶ መገለፅ ያለበት እኩይ ምግባራቸው ከጎንደር ከተማ አልፎ  ገደብየ ወደምትባል ከተማ ለማስፋፋት የሞከሩ ስርአት አልበኞች በህዝቡ ተቃውሞ ሙሉ ለሙሉ እንዲቆም የፈፀሙት ገድል የሚያኮራ ነው፡፡ በጎንደር ከተማና ደባርቅ አከባቢ ያለው ህዝብም የተፈጠረው መረጋጋት ተጠቅሞ ከአከባቢው አስተዳዳሪዎች ጋር መመካከር ጀምሯል፡፡

ህዝቡ በዚሁ ምክክሩ ለህግ ልኡላዊነት የተከፈለ የሰላማ ዜጎችና የፀጥታ ሃይሎች መስዋእትነት እውቅና በመስጠት በግለሰቦች ላይ እርምጃ በመውሰድ ህዝብን ከህዝብ ጋር ለማጋጨት የሞከሩ ግለሰቦችን እያወገዘ ይገኛል፡፡እናም የህዝቦች ግጭት ምኞት እንጂ እርግጠኛ ሆኖ አያውቅም-አይሆንምም የምንለው ለዚህ ነው፡፡ በአለማችን ህዝቦች በአደናጋሪ ፅንፈኛ ሃይሎች የተጨፋጨፉበት ታሪክ አይደለም አሁን የህግ ሉአላዊነት በሰፈነበትና ጠንካራ የህግ ማስከበርያ የመንግስት መዋቅሮች ባሉበት ትላንት ለዚህ ተግባር የሚገፋፉ አምባገነንና ዘረኛ መንግስታት በነበሩበት ዘመንም አልተከሰተም፡፡

ከፍም አለ ዝቅ ህገወጦች በፈፀሙት ህገወጥ ተግባር ከመጠየቅ የሚያድናቸው የለም፡፡ ይህ የፌደራል መንግስትና የአማራ ክልል በኮሙኒኬሽን ጉዳዮቻቸው በኩል ከሰጡት መግለጫ ቁልጭ ያለ መልእክት ተላልፋል፡፡ በተለይም የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ያሰመሩበት ጉዳይ ‘ በግርግር ውስጥ የፈፀምኩት ወንጀል ነውና አልጠየቅም የሚል አካል አይኖርም፡፡’ ህዝቡ በአብሮነቱ ፀረ ድህነት ትግሉ ያስቀጥላል፡፡

የሻእብያና ግንቦት ሰባት ተላላኪዎች የማህበራዊ ድረ ገፆች የግጭት ምኞት የመከነው እዛው ድረ ገፅ ባለ ውግያም ጭምር ነው፡፡  አሁን ወጣቱ ነቅቷል- ልታጋጩን አትችሉም ብሎ በበሳልና የላቀ እውቀት በፎቶግራፎች ጭምር አስደግፎ መልሶላቸዋል፡፡

በፌስ ቡክ ከተለቀቁት ድፍረት የተሞላባቸው ፀረ ትምክህተኞችና ጠባቦች መልእክቶችና ፎቶግራፎች መካከል የእሙየን ተስፋሁን ድንቅ ፎቶግራፍና መልእክት እንዳለ በማቅረብ ለዛሬ ልሰናበት፡፡ እናንተ ሚዛናዊና ደፋር ወጣቶች የነገዋ ተሰፋ ያላት ሀገር ተረካቢዎች ናቹህና በፀረ ትምክህት ትግላቹህ ቀጥሉበት፡፡በርቱ፡፡ ሰላም፡፡

We love each other and forever!! They’re my beloved friends from Gondar and me from Tigray but we are proud to be Ethiopians.Emoye

Leave a Reply