በጎንደር ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ ቅዳሜ ገበያ በተባለው ስፍራ የነበሩ ሱቆች ሙሉ በሙሉ ወደሙ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 6 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ በተለምዶ ቅዳሜ ገበያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ በስፍራው የነበሩ የአልባሳት የብረታ ብረትና የቅመማ ቅመም ሱቆች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተነገረ።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ትናንት ምሽት አራት ሰዓት ላይ የደረሰውን የእሳት አደጋ መንስኤ እያጣራ መሆኑን ገልጿል።

በገበያ ቦታው ከ400 በላይ ሱቆች እንደነበሩ የገለጹት የመምሪያው የህዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ኢንስፔክተር አበበ አለባቸው፥ በአደጋው የወደመው ንብረት ዝርዝር መረጃ እየተጣራ መሆኑን ተናግረዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ ሲሳይ አዳነ የከተማ አስተዳደሩ በአሁኑ ወቅት ተጎጅዎችን እንደገና ለማቋቋም ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።

የጎንደር ፋና ኤፍ ኤም ባልደረባችን ነብዩ ዮሃንስ በእሳት አደጋው በሰው ህይወት ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱን ዘግቧል። Source: FBC

Leave a Reply