በመዲናዋ አዳዲስ ሜትር ታክሲዎች ነገ አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን ከነገ ጀምሮ አዳዲስ ሜትር ታክሲዎች አገልግሎት ሊያስጀምር ነው።

ባለስልጣኑ እንዳለው 26 አክሲዮን ማህበራት እና ሶስት የግል ኩባንያዎች ተቋቁመው 1 ሺህ 163 ታክሲዎች ከቀረጥ ነፃ ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ ነው።

ከእነዚህ መካከል እስካሁን 836ቱ ሀገር ውስጥ መግባታቸውን ነው የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ይግዛው ዳኛው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት።

 

taxi_2.jpg

ታክሲዎቹን ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ለማድረግ ነገ በመስቀል አደባባይ የስምሪት መርሃ ግብር ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት ይካሄዳል።

ታክሲዎቹ በአለም አቀፍ ደረጃ ተሳፋሪው የሚሄድበትን ኪሎ ሜትር ልክ በማየት ክፍያ እንዲፈፅም የሚደረግባቸው ናቸው።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን የታሪፍ መጠኑን እየሰራ ሲሆን ስምሪታቸውም ከፍተኛ የትራንስፖርት እጥረት በሚታይባቸው አካባቢዎች ሀላፊው ገልፀዋል።

Source: FBC

 

 

Leave a Reply